Skip to content
Ethiopian Orthodox Gift Packages Englishአማርኛ
አጽዋማት

✞✞ ፆመ ፍልሰታ✞✞

(ጾመ ፍልሰታ) ፍልሰታ ፆም(ጾመ ማርያም) ሞት በጥር በነሀሴ መቃብር የፍልሰታ ፆም ከነሀሴ 1እስከ15 ነው ቤተ ክርስትያናችን እደሚገለፀው “እመቤታችን ያረፈችው ጥር 21ቀን ነው ሐዋርያት በድኗን ሊቀብሯት ወደ ጌተሰማኒ ይዘዋት ሲሄዱ አይሁድ አይተዋቸው በተኗቸው በዚህ ጊዜ መላእክት የእመቤታችንን አስክሬን ወስደው በገነት አኑረውታል በ8ወር በነሀሴ ሐዋርያት አስክሬኗን እንደገና ከጌታ ተቀብለው በፀሎትና በምህላ ቀብረዋታል በዚህ የቀብር ስነስርዓት ላይ ከ12 ሐዋርያት አንዱ ቶማስ አልነበረም።

ቅዱስ ቶማስ ከሀገረ ስብከቱ በደመና ተጭኖ ወደ እየሩሳሌም ሲመጣ ያገኛታል በዚህ ጊዜ ትንሳኤዋን ሌሎች ሐዋርያቶች አይተው ለእሱ የቀረበት መስሎት ተናዶ በፊት የልጅሽን ትንሳኤ ሳላይ ቀረው አሁን ደግሞ የአንቺን ትንሳኤ ሳላይ ቀርቼ ነበር ብሎ ከደመና ሊወረወር ቃጣው በዚህ ጊዜ እመቤታችን ቶማስን አፅናንታ ከእሱ በቀር ሌላ ትንሰኤዋን እንዳላየ ነገረችው።

ቶማስም ሐዋርያት ወዳሉበት እየሩሳሌም በደረሰ ጊዜ እመቤታችንን ቀበርናት ብለው ነገሩት እሱም አውቆ ምስጥሩን ደብቆ አይደረግም ሞት በጥር በነሀሴ መቃብር አላቸው ለማሳየትም መቃብር ሲከፍቱ አጧት በዚህ ጊዜ”እመቤታችን ተነስታ አርጋለች ብሎ ሁኔታውን ተረከላቸው ለምስክርም ይሆናል ብሎ የሰጠችውን (ሰበኗን) አሳያቸው ሰበኗንም ለበረከት ቆራርጠው ተከፋፍለው ወደ ሀገረ ስብከት ተበታትነዋል በዓመቱ ትንሳዬሽን ቶማስ አይቶ እንዴት እኛ ይቅርብን ብለው ከነሀሴ 1 ጀምሮ ሱባዬ ገቡ በነሀሴ14ቀንም ትኩስ በድን አድርጕ አምጥቶ ሰጣቸው ከቀበሯትም በጟላ በነሀሴ16 ተነስታለች በዚህ ቀን ጌታ ቀድሶ እመቤታችንም በልጇ እጅ ቆርባለች ከዚህ ጊዜ ጀምሮ የሐዋርያት ቤተክርስትያን የእመቤታችንን በረከት ለማግኘት ይህች ጊዜ ትፆማለች።

ለወዳጅ ዘመዶ የፍልሰታ ስጦታ ለመስጠት አጋፔን ይምረጡ።

Published August 9, 2026
Keep reading

More from the blog

All posts
Agape Blog

የቅድስና ሕይወት

ቅድስና የሚለው ቃል ቀደሰ ፤ አከበረ ፤ አነጻ ከሚለው የግእዝ ቃል የተገኘ ነው ፡፡ የቅድስና ባለቤት ምንጭ እና…

August 10, 2026 Read →

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *